Wednesday, April 8, 2020
Home > ዜና > የግብፁ መሪ ፕሬዝዳንት አልሲሲ በአገራቸው የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን እንደሚፈቱ ቃል ገቡ::

የግብፁ መሪ ፕሬዝዳንት አልሲሲ በአገራቸው የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን እንደሚፈቱ ቃል ገቡ::

የግብፁ መሪ አልሲሲ በሊቢያ በአሸባሪዎች የተገደሉ ኢትዮጵያዊያንን አፅም ወደ አገራቸው እንዲመለስ እገራችን እገዛ ታደርጋለች ብለዋል:: ፕሬዝዳንቱ ከዚህ በተጨማሪ በግብፅ አገር የታሰሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ለመፍታት ቃል ገብተዋል::

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በግብፅ ካይሮ ከፕሬዝዳንት አልሲሲ ጋር ባደረጉት ውይይት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የነበረን ጥርጣርሬ በማስወገድ በመተማመን ለመስራት መስማማታቸውን አስውቀዋል::

በመጨረሻም ከውይይቱ በኋላ ሁለቱ መሪዎች በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ መግለጫውን በአማርኛ ቋንቋ ሰጥተዋል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.