Friday, November 15, 2019
Home > ዜና > መንግስት የኦነጉ መሪ ለሰጡት መግለጫ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አለበት!

መንግስት የኦነጉ መሪ ለሰጡት መግለጫ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አለበት!

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር መከራም ሆነ ፈተና ብዙዎች ከሀዋሳው የኢህአዴግ ጉባዔ በሁዋላ ያበቃል ብለው ተስፋ አድርገው ነበር።የሕወሓት የስለት ልጅ የሆነው ኦነግ ትላንት አጋዚ የኦሮሞ ወጣቶችን ሰላማዊ የመብት እንቅስቃሴ ለማፈን ግንባር ግንባራቸውን ሲል ጥይት ያልተኮሰው ኦነግ ዛሬ ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ነው።

ለንጹሃን ሞትና ስደት ምክንያት መሆኑ ሳያንስ ማነው ትጥቄን የሚያስፈታኝ ብሏል።ይህ አደገኛ አካሄድ ልጆቹን ገብሮ እፎይ እላለሁ ላለው የኦሮሞም ሆነ የቀረው ሕዝብ ግጭት የሚጋብዝ በጠመንጃ ያልመጣን ስልጣን በጠመንጃ ለመንጠቅ ምክንያት የሚፈልጉ መንገድ የሚጠርግ ነው። በሕዝብ ሰላምና ደህንነት ላይ ቁማር መጫወት ክልክል ነው።

የሕግ የበላይነት ለማስከበር ዙሪያ ጥምጥም መሄድ አያስፈልግም።መንግስት የኦነጉ መሪ ለሰጡት መግለጫ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አለበት።የሕግ የበላይነት እንዲከበር በሰላማዊ መንገድ የጠየቁ ወጣቶችን በጅምላ ለማፈስ የሮጠ መንግስት በሰላም ስምምነት የተደመረው ኦነግን የጦርነት አዋጅ ዳር ዳርታ የሆነ መግለጫ ላይ ፈጥኖ ምላሽ ይስጥ። የሕግ የበላይነት ይከበር

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.