Wednesday, April 1, 2020
Home > ዜና > “ሁለት ቤቲዎችን አይቻላሁ”

“ሁለት ቤቲዎችን አይቻላሁ”

ከዚህ በፊት የቤቲንና የአብን ሊቀ መንበር ዶክተር ደሳለኝን ቃለ ምልልስ ስገመግም የቤቲ ጠንካራና ድፍረት የተሞላበት ያጠያየቅ ዘዴ በጣም ሊያስተቻት አይገባም ብዬ ሳትት አንዳንድ አንባቢዎች ቤቲ የተዛባና ወገናዊ ተለዋዋጭ ዘዴ ተጠቃሚ ናት የሚሉ ክሶች ተሰንዝረውባት ነበር። በምሳሌነት የተጠቀሰውም በቅርቡ ከጃዋር መሐመድ ጋር ያደረገችው ውይይት ባንጻራዊ ይታይ የሚል ጥቆማ ነበር።

የቤቲንና የጃዋርን ቃለ ምልልስ ለአንጻራዊነቱና ስለ እሷም የጋዜጠኝነት ስነ ምግባርና እኩላዊነት ለመገምገም ፕሮግራሙን ሙሉ ለሙሉ በአንክሮ ተመለከትኩ። ነገሩን ለማሳጠር ሁለት ቤቲዎች አይቻለሁ። የዶክተር ደሳለኝ ጠያቂ ፊቷም ያጠያየቅ ዘዴዋም አጥቂነትና ድፍረት የተሞላበት ነበር። ከጃዋርጋ ባደረገችው ቃለ ምልልስ ግን ቤቲ ካይናፋርነት ያላነሰና ባቀማመጧም ተሸጉጣ ጃዋርን እንዳታስቀይም ብዙ ተጨንቃ ልነጠፍ ለማለት የቃጣው የጀማሪ ጋዜጠኛ ገጽታ ያሳየችበት ሁኔታ ነበር ብል ብዙ ስህተት አይመስለኝም። ዶክተር ደሳለኝን ለማፋጠጥ ብዙ መረጃ ይዛ የቀረበችው ጋዜጠኛ ማለቂያ የሌላቸውን የጃዋርን አነጋጋሪ ነጥቦች ካለ አንድ ጊዜ በስተቀር ሳታነሳ ፕሮግራሟን መጨረሷ በእኔ አስተያየት ባለፈው ልጥፌ የሰጠኋትን ክብር በጣም ቀንሶታል።

ርቱእ ጋዜጠኛ እንደ ጥሩ ሐኪም ሁሉን ሰው እኩል ማየትና ሚዛናዊ አገልግሎት የማቅረብ ስነ ስርአት መከተል አለበት። ቤቲ በዚህ መስፈርት ከፍተኛ ድክመት አሳይታለች። ለቤቲ ይቅርታ ላደርግላት የምችለው ጃዋር በመንግስት ያፈቀደውን እንዲናገር ፈቃድ ያለው ስለሚመስል ቤቲ ማእቀብ ተደርጎብኝ ነው ካለች ይቅርታ ይገባት ይሆናል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.