Wednesday, April 8, 2020
Home > ዜና > ከ900 ሚሊዮን በር በላይ ከውጭ ጎብኝዎች የተሰበሰበ ገንዘብ የት ደረሰ??

ከ900 ሚሊዮን በር በላይ ከውጭ ጎብኝዎች የተሰበሰበ ገንዘብ የት ደረሰ??

በ2017 ወደ ኢትዮጵያ 800 ሽህ ገደማ የዉጭ ጎብኝወች መተዋል፡፡ ከዚህ ዉስጥ 80 በመቶዉ ላሊበላን ብለዉ የሚመጡ ናቸዉ ብሏል ትናንት የአማራ ቴሌቪዥን፡፡ ያ ማለት 640 ሺህ የሚሆኑት ላሊበላን ይጎበኛሉ ማለት ነዉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ላሊበላን ብለዉ የመጡ ላሊበላ ሳይደርሱ ሊመለሱ ይችላሉ፡፡ ከዚህ ዉስጥ 40 ሽህ እናንሳለት፡፡ 600 ሺህ ቀረ፡፡ የመግቢያ ዋጋዉ ለአንድ ሰዉ 50 ዶላር ነዉ፡፡ 600 መቶ ሽህ ሰዉ በ 50 ዶላር ስናሰላዉ ወደ 30 ሚሊየን ዶላር በአመት ገቢ አለዉ፡፡ 900 ሚሊየን ብር አካባቢ ማለት ነዉ፡፡የሀገር ዉስጥ ጎብኝዉን ትተነዉ ነዉ፡፡ ይሄ ገንዘብ የት ነዉ የተወሰደዉ?? በነገራችን ላይ ይሄ በሚዋጣ ገንዘብ የሚሰራ አይደለም፡፡ ለ 1ቢሊየን የሚጠጋ አመታዊ ገቢ ያለዉ ቅርስ እንኳን እራሱን የሀገሪቱን ቅርሶች ለመንከባከብ ከበቂ በላይ ነዉ፡፡ ይሄን መንግስት እስከዛሬ የበላዉ ይበቃዋል አሁኑኑ ከካዝና አዉጥቶ በፍጥነት ቅርሱን ማዳን አለበት፡፡

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ገቢ 2/3ተኛዉ ከአማራ ክልል የሚገኝ ነዉ፡፡ ከዉጭ የሚላከዉ እስከ 5 ቢሊየን የሚደርሰዉ ዶላር ከግማሽ በላይ የሚመጣዉ ከ 2 ሚሊየን በላይ በምእራቡ አለም እና በአረብ አገራት የሚኖረዉ የአማራ ህዝብ ነዉ፡፡ ወደ ዉጭ የሚላከዉ ጥራጥሬ፤ የቅባት እህል፤ የቀንድ ከብት፤ ማእድን (ለምሳሌ ኦፓል)፤ አትክልትና ፍራፍሬ እና የመሳሰሉት የሀገሪቱን ከ 60 በመቶ ባለይ የዶላር ምንጭ ይሸፍናል፡፡ከተለያዩ ሀገራት የምንበደረዉ ብድር እና እርዳታ ደግሞ አለ፡፡ ለዚህ ሁሉ የገቢ ምንጭ የሆነዉ የአማራ ህዝብ እንዴት ነዉ የቅርስ ማስጠገኛ ገንዘብ ያጣዉ፤ ከ1ሺህ በላይ የዳስ ትምህርት ቤት ያለዉ፤ የሃገሪቱ ደሃ ህዝብ የሆነዉ፤ አንዲትም ፋብሪካ የሌለዉ፤ አንድም ትልቅ ፕሮጀከት (የባቡርም ሆነ የመንገድ) የሌለዉ፡፡

ባለፈዉ አመት ለብአዴን ጠቆም ያረግነዉ አንድ ስትራቴጅ ነበር እሱም ክልሎች በሚያስገቡት ገቢ ልክ የሚገኘዉን ዶላር ፕሮፖርሽናሊ እንዲከፋፈሉ ነዉ፡፡ ወይ የንግድ ፖሊሲዉን (በፌደራል ጁርስዲክሽን ያለዉን) ቀይሮ ክልሎች የራሳቸዉን ንግድ እንዲያስኬዱ ማድረግ አለበለዚያ በየክልሉ ዉስጥ የሚገኘዉ ሪሶርስ እና የሚያስገባዉ ገቢ ተሰልቶ ለክልሎች መሰጠት አለበት፡፡ የፌደራል መንግስት ለስራ ማስኬጃ ብቻ ያስቀር እንደሆን እንጅ ሁሉንም ገቢ ይዞ የሚፈለገዉ አካባቢ ብቻ የፋብሪካ መንደር ሊገነባ አይችልም፡፡ ለምሳሌ የሶማሌ ክልል ነዳጅ ተገኘ አሁን ያለዉ ስምምነት የነዳጁ የተወሰነዉ ገቢ ለክልሉ ይዉላል የሚል ነዉ፡፡ ለጤፉም፤ ለመብራቱም፤ ለሰሊጡም፤ ለኦፓሉም፤ ለቁም እንስሳቱም፤ ለአትክልትና ጥራጥሬዉም ይህ ህግ ሊሰራ ይገባል፡፡ ፍብሪካ ሲተከል ባብዛኛዉ ማሽኑ በዶላር ተገዝቶ ነዉ፡፡ ይህ ማለት አማራ በአማካኝ ከ 60 በመቶ በላይ ለሀገሪቱ ዶላር አመንጭ ሆኖ ፍብሪካ እና ሌሎች ትልልቅ ፕሮጀክቶች ግን የሚገነቡት የአማራ ህዝብ በማይደርስባቸዉ አካባቢወች እና ክልሎች ነዉ፡፡ የአማራ ህዝብ ፍብሪካ እና ትልልቅ ፕሮጀክቶች እንዲኖሩት ከተፈለገ የምናስገባዉ ዶላር ተቆጥሮ መሰጠተት አለበት፡፡እኛ ገንዘቡን እናዋጣለን ፋብሪካዉን ሌላ ቦታ ይተክሉታል፡፡ ይሄ አያስኬድም፡፡ ይህ ጥሩ የመደራደሪያ ሃሳብ ነዉ የክልሉ መንግስት ሊያስብበት ይገባል፡፡

በሚኪ አማራ(Miki Amhara)

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.