Wednesday, April 1, 2020
Home > ዜና > ሰለ የደም ግፊት(HYPERTENSION) ምን ያህል ያውቃሉ?

ሰለ የደም ግፊት(HYPERTENSION) ምን ያህል ያውቃሉ?

#የደም_ግፊት ማለት ልባችን ደምን ወደ ተለያዩ ክፍሎች ለማሠራጨት ሲል በደም ቧንቧዎች ላይ የሚፈጥረው ግፊት ሲሆን ልኬቱም በ2 ቁጥሮች ይገለጻል፡፡

የላይኛው ልኬት ሲስቶልክ ሲባል የሚፈጠረውም የልብ ጡንቻዎች በሚኮማተሩበት እና ደምን በሚረጩበት ጊዜ ሲሆን የታችኛው ልኬት ደግመ ዳይስቶልክ ወይም የተኮማተሩ የልብ ጡንቻዎች ሲለጠጡ የሚፈጠር ግፊት ነው፡፡ ትክክለኛ የግፊት መጠን የሚባለው የግፊት ልኬት መጠን ሲስቶሊኩ ከመቶ ሃያ በታች እንዲሁም ዲይሰቶሊኩ ከሰማኒያ በታች ሲሆን ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የግፊት መጠን በተለያዩ ምክንያቶች ሊዛባና ከዚህ ትክክለኛ የግፊት መጠን ሊጨምር ይችላል፡፡

ተ.ቁ መግለጫ

( BP classification )

1 ትክክለኛው የደም ግፊት መጠን < 120 < 80

2 ቅድመ ከፍተኛ የደም ግፊት መጠን 120 – 139 80 – 89

3 የመጀመሪያ ደረጃ ከፍተኛ የደም ግፊት መጠን 140 – 159 90 – 99

4 ሁለተኛ ደረጃና ከፍተኛ የደም ግፊት መጠን ≥ 160 ≥ 100

የደም ግፊት ምልክቶች:-

ይህ በሽታ አብዛኛውን ጊዜ ምልክቶችን በግልፅ የማያሳይ ሲሆን ሕሙማን ለሌላ የጤና ችግር ወደ ጤና ተቋማት ሲሄዱ በአጋጣሚ በሕክምና በባለሙያ ምርመራ የሚገኝ የበሽታ ዓይነት ነው፡፡

✔በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰት ከባድ የራስ ምታት

✔በትክክል አለማየት ሁኔታ

✔ማቅለሽለሽና ማስመለስ

✔ተደጋጋሚ ነስር ወይም በአፍንጫ ደም መፍሰስ

✔የማዞር እና ማጥወልወል ስሜት

የደም ግፊት ዓይነቶች

1, የመጀመሪያ ደረጃ የደም ግፊት የመጀመሪያ ደረጃ ደም ግፊት ምክንያቱ በግልፅ ብዙም አይታወቅም ሆኖም በተለያዩ መንስዔዎች ምክንያት

ይፈጥራል፡፡ በተለይም ዘረ-መል (Gene) ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ለውጦች እንደ ምክንያትነት ይቀርባሉ ነገር ግን በተጨባጭ የትኛው ዘረ-መል (Gene) ችግሩን ያስከትላል የሚለው ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አላገኘም፡፡

2, ሁለተኛ ደረጃ ደም ግፊት የዚህ ደም ግፊት ዓይነት መንስዔዎቹ በግልፅ የሚታወቁ ናቸው፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መንስዔዎች መከላከል

እና መቆጣጠር ደም ግፊቱንመቆጣጠር ይቻላል፡፡

✔በኩላሊትና በአካባቢው በሚገኙ የደም ቧንቧዎች ላይ የሚከሰት የጤና ችግር

✔በከፍተኛ ውፍረት ምክንያት አላስፈላጊ የስብ ክምችት

✔የስኳር ሕመም

✔እርግዝና ወቅት የሚከሰት የደም ግፊት ከሕክምና ባለሙያጋር በማነጋገር

✔ከፍተኛ መጠን ያለው አልኮል በየቀኑ መጠጣት

✔ሲጋራ ማጨስ

✔ለተለያዩ በሽታዎች የሚወሰዱ መድኃኒቶች የደም ግፊት መጠንን ሊጨምሩ ይችላሉ፡፡ በተለይም ስትሮይድስ(Steroids)

✔የተከለከሉና አደገኛ ዕፆችን ችግሩን መጠቀም

✔በምግብ ላይ ከመጠን ያለፈ ጨው መጠቀም

#የደም_ግፊት_ምርመራ

የደም ግፊት ልኬት በተደጋጋሚ መደረግ ያለበት ሲሆን ተመሳሳይ ውጤት ከተገኘ ችግር እንደተከሰተ አመልካች ነው፡፡

በአንድ ጊዜ ልኬት ብቻ የደም ግፊት አለ ብሎ ለመወሰን አስቸጋሪ ነው፡፡

#የደም_ግፊት_የሕክምና_መንገዶቹ

1.ከመድኃኒት ውጭ ሕክምና

የደም ግፊት መጠንን አስቀድሞ እንዳይከሰት ለመከላከል የሚረዱ የተለያዩ አማራጭ መንገዶች ያሉ ሲሆን ከእነዚህምመካከል፡፡

☞ከፍተኛ የሰውነት ክብደት በመቀነስ

☞የሰውነት እንቅስቃሴ በማድረግ

☞የምንወስደውን የጨው መጠን በመቀነስ

☞ከፍተኛ የአልኮል መጠንን መቀነስ፣ ጫት አለመቃም፣ ሲጋራ ባለማጨስ፣ ሌሎች የሚያነቃቁ ንጥረ ነገሮችን በብዛት አለመውሰድ

☞መጨነቅን መቀነስ

☞የደም ግፊት በሽታን የሚያመጡ ተያያዥ የጤና ችግሮችን ማስወገድ፡፡

2.የመድኃኒት ሕክምና

የደም ግፊት መቆጣጠሪያ መድኃኒት ማለት የደም ግፊትን በመቆጣጠር በሽታው ሊያመጣ የሚችለውን ጉዳት ወይም ሞት መቀነስ የሚችሉ ናቸው፡፡ መድኃኒቶቹም በትክክለኛ የሕክምና ባለሙያ የሚታዘዙ እና በዓይነት እና በመጠን በየጊዜው እንደ ሕሙማን የሕመም ደረጃ ይለያያሉ፡፡

የሚታዘዘው የመድኃኒት መጠን እና ዓይነት ከሕመሙ ደረጃ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት ያለውና ይህንን ሁኔታ ለማስተካከልና ለመቆጣጠር በየጊዜው በጤና ተቋማት በመገኘት የጤና ክትትልን ማድረግ ይኖርብናል፡፡ በሽተውን ለመቆጣጠር በመጀመሪያ ደረጃ ከምንጠቀማቸው መድኃኒቶች ውስጥ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፣

1.አንጆ ቴንሲን ኮንቨርቲንግ ኢንዛይም ኢቲቢተርስ(Angiotensin converting enzymeinhibitors)ለምሳሌ ኢናላፕሪል፣ሊስኖፕሪል እና የመሳሰሉት በዚህ የመድኃኒት ክፍል ውስጥ

ይካተታሉ፡፡

2.ካልሲየም ቻናል ብሎከር (Calcium channel blocker)፡-

ይህ ዓይነት መድኃኒት እንደ ኒፊዲፒን፣ አሚሎዲፒን እና የመሳሰሉትን የሚያጠቃልል ሲሆን ካልሲየም የተባለውን ንጥረ ነገር ወደ ሴሎች እንዳይገባ በማድረግ ግፊትን ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡

3.ዳዩሪቲክስ (Diuretics)፡-

በተለይ ታያዛይድ የሚባለው መድኃኒት ለምሳሌ ኃድሮክሎሮታያዛይድ (HCT) በሽንት መልክ ውኃና ንጥረ ነገሮች በተለይ ፖታሲየም የተባለውን ንጥረ ነገር እንዲወገድ በማድረግ ግፊትን ለመቆጣጠር ያገለግላል፡፡

4.ቤታ ብሎ ከርስ (Beta-blockers)፡-

ይህ ዓይነት መድኃኒት የልብ ምት፣ የሬኒን መመረት፣

የኖርኢፕንፊን ተግባርና የመሳሰሉት በመቀነስ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር ያገለግላል፡፡ ለምሳሌ ፕሮፕራኖሎል፣ አቴኖሎል፣ሜቶፕሮሎልና የመሳሰሉት

5.ሐይድራላዝን (Hydralizine)፡-

ይህ ዓይነት መድኃኒት የደም ቧንቧዎችን በማስፋት (Dilating

arteries) የደም ግፊትን ለመቆጣጠር የሚያገለግል መድኃኒት ነው፡፡

☞ሁሉም መድሀኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት መዘንጋት የለበትም።

☞የጎንዮሽ ጉዳት ሲያጋጥምመድኃኒቱን ሳያቋርጡ ለጤና ባለሙያ መናገር ያስፈልጋል፡፡

☞መድኃኒቱን ሕጋዊ ፍቃድ ካላቸው ተቋማት መግዛት ይገባል፡፡

☞ስለ መድኃኒት አወሳሰድ የጤና ባለሙያን በሚገባ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.