Wednesday, April 8, 2020
Home > ዜና > “ዶክመንቶቹ የወጡት በአቶ ተወልድ ትእዛዝ ነው” ጋዜጠኛ አበበ ገላው

“ዶክመንቶቹ የወጡት በአቶ ተወልድ ትእዛዝ ነው” ጋዜጠኛ አበበ ገላው

በኢትዮጵያ አየር መንገድ በአብራሪነት በማገልገል ላይ እያለሁ በማንነቴ ምክንያት ተደጋጋሚ ጥቃት፣ ተጽእኖና አድልኦ ስለተፈጸመብኝ ከባርነት ነጻነትን መርጨ በግብርና ስራ ተሰማራሁ በማለት በአየር መንገዱ ውስጥ ለበርካታ አመታት በህወሃቱ ታማኝ አባል አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም አመራር የሚፈጸመውን ህገወጥ አሰራርና በደል ያጋለጠውን ካፕቴን ዮሃንስ ተስፋዬን አስመልክቶ አየር መንገዱ ትናንት አጭር መግለጫ አውጥቶ ነበር።

መግለጫው በአየር መንገዱ የሰፈነውን አድሏዊ አሰራር ለማድበስበስ የሞከረ መሆኑ ግልጽ ነው። በአየር መንገዱ “ዜጋ” እና “ዜጋ ያልሆኑ” እነማን እንደሚባሉ ያደባባይ ሚስጥር ነው።

ዛሬ ደግሞ ይባስ ብለው አየር መንገዱ የካፕቴን ዮሃንስን የስልጠና ዶክመንቶች ህገ ወጥ በሆነና ሃላፊነት በጎደለው መንገድ ፌስቡክ ላይ አውጥተዋል።

ምንም እንኳን ካፕቴን ዮሃንስ ስልጠናውን አጠናቆ በስራ ላይ የነበረ ቢሆንም ያወጡት በስልጠና ወቅት የተሰጡ ጥቃቅን አሉታዊ የአሰልጣኝ አስተያየት ነው። ከአየር መንገዱ ምንጮች እንደተራዳሁት ዶክመንቶቹ የወጡት በአቶ ተወልደ ትዛዝ ነው።

አቶ ተወልደ ጠንካራ የነበረውን የሰራተኛ ማህበር አፍርሰው የዘር፣ የዝምድናና የጥቅም ሰንሰለት መዘርጋት ብቻ ሳይሆን አየር መንገዱን ከተለያዩ ካምፓኒዎችና ሸሪኮች ኮሚሽን እየተቀበሉ እጅግ ከፍተኛ እዳ ውስጥ መክተታቸው ይነገራል።

የሚመለከተው የበላይ አካል የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ ሊመረምረውና ከላይ እሰከታች የተንሰራፋውን ህገወጥነትና ሙስና ለማስቆም እርምጃ መውሰድ ይገባዋል።

የእነ ተወልደ ጭቆና አክትሞ ዜጎች ሁሉ በአገራቸው መብታቸው እኩል ሊረጋገጥላቸው ይገባል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.