Wednesday, April 1, 2020
Home > ማህበራዊ > ሴት ልጅ ወሲብ ስትፈጽም መጨረስ አለመጨረሷን በምን እናውቃለን?

ሴት ልጅ ወሲብ ስትፈጽም መጨረስ አለመጨረሷን በምን እናውቃለን?

በውስጥ መልእክት በብዛት ከሚመጡልን ጥያቄዎች አንዱ “ሴት በወሲብ ግዜ መጨረስ አለመጨረሷን እንዴት እናውቃለን?” የሚል ነው። መልሱ ቀላል ነው። ሴት ልጅ በወሲብ እርካታ ጫፍ ላይ ስትደርስ ትንፋሿ ይጨምራል፣ ሰውነቷ በሙሉ ይወጣጠራል፣ ብልቷ በጣም ይጠብቃል (አንዳንዴ ለወንዱ እንቅስቃሴ እስከሚያስቸግር ድረስ)፣ አጥብቆ ማቀፍ ወይም ትራስ የመሳሰሉትን ነገሮች ጨምድዶ መያዝ፣ መለፍለፍ ወዘተ ሲሆኑ ልክ ስሜቷን ስትጨርስ ደግሞ የብልት ፈሳሽ መብዛት፣ መዝለፍለፍ፣ የብልት መላላት፣ እንቅስቃሴ መቀነስ፣ ከራስዋ ስሜት በመውጣት የወንዱን ስሜት ማንበብ ወይም መጠየቅ፣ ሳቅ ማብዛት፣ ፍቅሯን በልዩ ቋንቋ መግለጽ ወዘተ ናቸው።

አንባብያን ማወቅ የሚገባቸው ነገር ግን ሁሉም ሴቶች በወሲብ ሲረኩ ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ሁሉ ያሳያሉ ማለት አይደለም። ነገር ግን በከፊል ወይም በአብዛኛው ሊያሳዩ የሚችሉ ሴቶች እንዳሉ መረዳት ያስፈልጋል።

ሴቶች እንደሁኔታው ወንዱን ለማስደሰት ወይም በሌላ ማንኛውም ምክንያት ሳይጨርሱ እንደጨረሱ ማስመሰል በጣም የተለመደ ተግባር ነው። ወንዶች ይህንን ሁኔታ በመረዳት ሴቶችን መጀመሪያ ለማስጨረስ መሞከር ይኖርባቸዋል።

በዶ/ር አንተነህ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.