Friday, April 10, 2020
Home > ዜና > አስደሳች ዜና – ዶክተር አብይ ታሪክ ሰሩ አንብበው ሼር በማድረግ ያጋሩ

አስደሳች ዜና – ዶክተር አብይ ታሪክ ሰሩ አንብበው ሼር በማድረግ ያጋሩ

ዶክተር አብይ ታሪክ ሰሩ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ 50 ከመቶ ሚኒስትሮቿ ሴቶች አርገው ሾመዋል። ሀገሪቱ በቀውስ ውስጥ ስትሆን ከወታደር በላይ ለሰላም የተጉ፣ ከሌብነት የፀዱ መሆናቸው፣ ባስቀመጥነው አቅጣጫ መሠረት ሴቶች ግማሹን ቦታ እንዲይዙ ተደርጓል፡፡

ከሌብነት የፀዳ አገልግሎት፣ ቅንነት፣ አገልጋይነት ሕዝቡ የሚጠብቅባቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር. ዐብይ ለአዳዲሶቹ የሚኒስትር ዕጩዎች አሳስበዋል፡፡

ተቋማዊ ሪፎርም በመሥራት የሥራ ቦታውን የሚያጸዱና ምቹ የሥራ አካባቢ የሚፈጥሩ፣ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመቀናጀት በቴክኖሎጂ ታግዘው የሚሠሩ፣ ከሠራተኛ ቀድመው ወደ ሥራ የሚገቡና ዘግይተው የሚሠሩ እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡

የሰውን ችግር መረዳት፣ ቁጡ አለመሆን፣ ሠራተኞችን ደስተኛ የሚደርጉ እንዲሆኑ፣ የአለባበስ ሥርዓት የሚያስጠብቁና አሠራር የሚገሩ እንዲሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ስብሰባ መቀነስ፣ ባጠረ ሰዓት ተግባብቶ ወደ ሥራ መግባት፣ በዕቅድና ሪፖርት ላይ በአግባቡና ባጠረ ጊዜ መወያዬት፣ ምክር ቤቶች ለክትትል ሲመጡ ኮርተው የሚመለሱበት፣ ሕዝብ በአገልግሎቱ የሚረካበት ተቋም እንዲፈጥሩም ዶክተር ዐብይ አስረድተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ 50 በመቶ የሚኒስትር ምክር ቤታቸውንም በሴቶች አስይዘውታል፡፡ኢትዮጵያም 50 በመቶ ሚኒሰትሮቿን ሴቶችን አድርጋለች፡፡

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.