Wednesday, April 8, 2020
Home > ዜና > አየር መንገድ ከ41 ዓመት ቦሐላ ሊጀምር ነው ዝርዝሩን ያንብቡ

አየር መንገድ ከ41 ዓመት ቦሐላ ሊጀምር ነው ዝርዝሩን ያንብቡ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ 41 ዓመት አቋርጦት የነበረውን ወደ ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በረራ ሊጀምር ነው። አየር መንገዱ ወደ ሞቃዲሾ የሚያደርገውን በረራ ከሁለት ሳምንት በኋላ በፈረንጆቹ ህዳር 2 2018 ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም፥ አየር መንገዱ ላለፉት አራት አስርት አመታት አቋርጦት የቆየውን በረራ በድጋሜ በመጀመሩ ደስተኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያና ሶማሊያ መንግስታትም ለበርካታ ዓመታት በሀገራቱ መካከል ተቋርጦ የቆየው በረራ እንዲጀምር ላደረጉት ድጋፍ ዋና ስራ አስፈፃሚው ምስጋና አቅርበዋል።

በረራው የሁለቱን ሀገራት የህዝብ ለህዝብ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ከፍ ያለ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም አስታውቀዋል።

ከዚህ ባለፈ በአሜሪካ፣ አውሮፓ ፣ኢስያ፣መካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ሀገራት የሚኖሩ ሶማሊያውያን ዲያስፖራዎች 116 በሚሆኑ የአየር መንገዱ መደራሻዎች ወደ ሀገራቸው መብረር እንዲችሉ ይረዳል ብለዋል።

አየር መንገዱ ወደ ሞቃዲሾ የሚያደርገውን የየእለት በረራ እንደሚያሳድገው የገለፁ ሲሆን፥ ይህ በረራም ለሁለቱ ሀገራትና ለአለም አማራጭ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ምንጭ ፋና ብሮድካስቲንግ ሼር በማድረግ ያጋሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.