Monday, March 30, 2020
Home > ዜና > የኢትዮጵያ መንግስት በሚስጢር 23 ሄክታር መሬት ለሱዳን መስጠቱ ታወቀ! – DW

የኢትዮጵያ መንግስት በሚስጢር 23 ሄክታር መሬት ለሱዳን መስጠቱ ታወቀ! – DW

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ልዩ ረዳት እና የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብይ ኤፍሬም ለ «DW» እንዳብራሩት ህጋዊ ተቀባይነት በሌለው ስምምነት ከአማራ ክልል ተላልፈው የተሰጡት መሬቶች በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲመለሱ የሚያደርግ ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራውን ጀምሯል።

የቀድሞ የመተማ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሙሉዓለም ገሌ በበኩላቸው ገዥው የኢህአዲግ መንግስት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ስልጣኑን የሚቀናቀኑ በሱዳን ድንበር አካባቢ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ትጥቅ ያነሱ ተቃዋሚ ኃይላትን ለማጥፋት ከጥንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት ስር የነበረው ከ 23 ሺህ ሄክታር የሚልቅ የመተማ ደለሎ ለም የእርሻ መሬት ከ 12 ኪሎ ሜትር በላይ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በመዝለቅ ለሱዳን አሳልፎ ሰቷል ሲሉ ወቅሰዋል። የቀድሞ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የነበሩት ባለስልጣን መሬቱ ለሱዳን ተላልፎ እንዲሰጥ ባቀረቡት ሰነድ ላይ አልፈርምም ካሉ በኋላ በማያውቁት ጉዳይ 38 የተለያዩ ክሶች ተመስርቶባቸው ከ 4 ዓመታት በላይ መታሰራቸውንም አቶ ሙሉዓለም ገልጸዋል ።

የኢትዮጵያ መንግስት በሚስጥራዊ ስምምነት ከ 23ሺህ ሄክታር በላይ መተማ ደለሎ የሚገኘውን የአገሩን መሬት ቆርሶ ለሱዳን ሰቷል በሚል በአካባቢው የሚኖሩ አርሶአደሮች በተቃውሞ ጎራ የተሰለፉ የፖለቲካ ድርጅቶች አክቲቪስቶች እና የኢትዮጵያ የድንበር ጉዳይ ኮሚቴ በሚል የተቋቋመ ገለልተኛ ድርጅት ጭምር ሲያቀርቡ ለነበረው ተደጋጋሚ ክስ የአገሪቱን ሰላም ለማወክ የሚጥሩ ጸረ ሰላም ሃይሎች የፈጠራ ክስ ነው በማለት ሲያጣጥለው ቀይቷል።

የአዴፓ አመራሮችም ሆኑ የፌደራል መንግሥት ባለስልጣናት በ 1988 ዓ.ም በሁለቱ አገራት መካከል በተካሄደው የድንበር ግጭት ገፍተን ከያዝነው የሱዳን መሬት ለቀን ወተናል እንጂ የሰጥነው መሬት የለም በማለት ማስተባበላቸው አይዘነጋም።

ይሁን እንጂ እንደ ሱዳን ትሪቡን ያሉ የዜና አውታሮች እ.ኤ.አ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በተለይም በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አቅራቢያ በአትባራ ወንዝ ዙሪያ የሚገኙ የምሥራቃዊ ሱዳን ገበሬዎች ከ 100 ዓመታት በላይ አወዛጋቢ ሆነው የቆዩ የእርሻ መሬቶቻቸው እንደተመለሱላቸው የሚገልጹ ዘገባዎችን በሰፊው ሲያሰራጩ ቆይተዋል።

የመሬቱን ለሱዳን ተላልፎ መሰጠት የተቃወሙ ገበሬዎች በጎንደር እና ማዕከላዊ እስርቤቶች የሽብር ክስ እየተመሰረተባቸው ሰቆቃ እንደተፈጸመባቸውም ይነገራል። የአማራ ክልል የጸጥታ እና ደህንነት ሃላፊ በነበሩበት ወቅት ከሱዳን መንግስት ጋር ምስጢራዊውን ስምምነት ተፈራርመዋል እየተባለ ትችት ሲሰነዘርባቸው የቆዩት የአዴፓ የወቅቱ ሊቀመንበር እና የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቅርቡ ከአማራ ቴሌቪቭን ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ስምምነቱ በተፈጸመበት ወቅት ለትምህርት እንግሊዝ ሃገር እንደነበሩ እና ሆን ተብሎ ስማቸውን የማጥፋት ዘመቻ ሲካሄድ መቆየቱን በመግለጽ ተላልፎ የተሰጠው መሬት ከጥንት ጀምሮ በኢትዮጵያ የግዛት ሉዓላዊነት ስር እንደነበረ ሲሰሙ በተፈጸመው ታሪካዊ ስህተት ክፉኛ መደንገጣቸውን ነበር የገለፁት::

አዘጋጅ መምህር ስዩም ተሾመ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.