Monday, March 30, 2020
Home > ዜና > ዶ/ር አምባቸው መኮንን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ሊሾሙ ነው! – ESAT

ዶ/ር አምባቸው መኮንን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ሊሾሙ ነው! – ESAT

ዶ/ር አምባቸው መኮንን የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ሊሾሙ ነው ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 09 ቀን 2011 ዓ/ም ) የብአዴን ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር አምባቸው በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚሾሙ ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። ዶ/ር አምባቸው ፕሬዚዳንት ሆነው ለማገልገል ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውንና ፓርቲያቸው ጥያቄያቸውን ላለመቀበል ተቸግሮ እንደነበር የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

የአዴፓ መሪዎች ምን ይላሉ?

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔ አለም ከዚህ በታች ያለውን ፅሁፍ በገፁ አስፍሯል:

ሰሞኑን ከሚኒስትሮች ሹመት እና ከዶ/ር አምባቸው መኮንን ጋር በተያያዘ አዴፓ ( ብአዴን) ከፍተኛ ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል። በእነዚህ ሁለት ጉዳዮች ዙሪያ በቅርብ ከማውቀው የድርጅቱ ቁልፍ ሰው ጋር ውይይት አድርጌ ነበር። የነገረኝን እንደወረደ አቀርበዋለሁ። (ልብ በሉ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የእኔ አስተያየት አልተካተተበትም።)

1ኛ- ዶ/ር አምባቸውን በተመለከተ

“ዶ/ር አምባቸው ፕሬዚዳንት ለመሆን ጥያቄውን ያቀረቡት ራሳቸው ናቸው። ጥያቄውን እንዳቀረቡ አቶ ገዱና አቶ ደመቀ በጽኑ ተቃውመዋቸዋል። አንተም ልትከዳን ነው በሚል ማንገራገሪያ ሳይቀር ውሳኔያቸውን እንዲያጤኑት ለምነዋቸዋል። ዶ/ር አምባቸው፣ ‘በዚሁ ቦታ ብሆን፣ ትንሽ ጊዜ ወስጄ ለማንበብና ለሌሎች የሃላፊነት ቦታዎች ራሴን ለማዘጋጀት ይጠቅመኛል’ የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል። ይህም ተቀባይነት ባለማግኘቱ ‘ እንደሱ ከሆነ የፕሬዚዳንቱ ስልጣን በአዋጅ ትንሽ ከፍ ይደረግና ኢንቨስትመንትን በመሳብ እና በዲፕሎማሲው ስራ በስፋት የምሳተፍበት ሁኔታዎች ይመቻቹልኝ’ ብለው ሃሳብ በማቅረባቸው በዚህ መሰረት ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቷል። ምናልባትም ሰኞ ፕሬዚዳንት ሆነው በይፋ ሊሾሙ ይችላሉ። በአቶ ገዱና አቶ ደመቀ ላይ ሲዘንብ የነበረው ትችት ተገቢ ያልሆነና በመረጃ ላይ ያልተደገፈ ነው።”

ማስታወሻ- ዶ/ር አምባቸውን ስላላነጋገርኳቸው የእርሳቸውን አስተያየት ማካተት አልቻልኩም። በእርሳቸው በኩል ያለውን አስተያየት ካገኘሁ አቀርባለሁ።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.