Saturday, February 29, 2020
Home > ዜና > ሐረር ውስጥ የተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ በ Veronica Melaku የቀረበ አስተያየት!

ሐረር ውስጥ የተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ በ Veronica Melaku የቀረበ አስተያየት!

የዛሬውን ፅሁፌን የምጀምረው ዘመን አይሽሬ በሆነው ኢትዮጵያዊ ሊቅ ገብረህይወት ባይከዳኝ ስለ ህግና ስርአት ከ 1 መቶ አመታት በፊት ከፃፈው መፅሀፉ በቀነጨብኩት ድንቅ አባባል ነው ።

ገብረህይወት በ19ኛው ክዘ መጨረሻ ኢትዮጵያውያንን በመከረበት መፅሀፉ እንደሚከተለው ይላል…

” አእምሮ የሌለው ህዝብ ሥርአት የለውም። ሥርአት የሌለው ህዝብም የደለደለ ሀይል የለውም ። የሀይል ምንጭ ስርአትና ህግ ማክበር ነው እንጅ የሰራዊት ብዛት አይደለም። ስርአት ከሌለው ሰፊ መንግስት ይልቅ ትንሽ ከተማ ሞያ ትሰራለች።” ይላል።

አሁን በዚህ በአለንበት ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ በጣም እየተቸገረ ያለው ህግና ስርአት አፈር ድሜ በመብላቱ ነው ። ዛሬ ዘግይቼ SHGER FM 101 ስለሀረር የሰራውን ዜና አዳምጨ በጣም ዘገነነኝ። እረ ምን ጉድ ነው? የሐረር ከተማ ህዝብ ቄሮ በሚባሉት ሽፍታዎች ውሃ ከተከለከለ 6 ወራት አለፈው ” ይላል ።

ዜናው ይቀጥልና ” ችግሩን ለመፍታት ከቄሮ ፣ ከመንግስት ተወካዮችና ከአባገዳዎች የተወጣጣ ቡድን ችግሩን ለመፍታት ቢጥሩም አልተሳካም ” ይላል።

ይሄኛውን ቀልድ ስሰማ ብብቴ ውስጥ የኮረኮሩኝ ያክል ከትከት በማለት ሳቀሁኝ። 🙂 የችግሩ ፈጣሪ ቄሮ የሚባል ቡድን ሆኖ እያለ ከቄሮ ጋር በመመካከር ችግሩን ለመፍታት ጥረት ቢደረግም አልተቻለም ብሎ መቀለድ በሬ ጠፍቶብህ በሬህን ከሰረቀህ ሌባ ጋር በሬህን ፍለጋ እንደመሰማራት ማለት ነው።

እረ ለመሆኑ ህግና ስርአት ባለበት አገር በደቂቃ ውስጥ በህግ ማስከበር እርምጃ የሚፈታ ችግርን 6 ወራትን ለምን ሊወስድ ቻለ? ክልሉ እንደዚህ የስርአት አልበኞች መናሃሪያ ሲሆን እና ህዝብ ፍዳውን ሲያይ እንደት መንግስት ዝም ሊል ቻለ?

አሁን በተጨባጭ የዚህ መንግስት ፈተና እየሆነ ያለው ሌላው ክልል ሳይሆን ኦሮሚያ የሚባለው ክልል ነው።

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ለሚኖሩ የሌሎች ብሄር ተወላጆችና ህግ አክባሪ ኦሮሞዎች አዝንላቸዋለሁኝ። ኦሮሚያ ክልል ማለት ህግና ስርአት የሌለበት ፣ ቄሮ የሚባል ቡድን የፈለገውን የሚያደርግበት ፣ ደም የሚያፈስበት ፣ ንብረትን የሚዘርፍበት ፣የፖሊስን መዋቅር አፈራርሶ የሚፈነጭበት በሌላ በኩል የኦነግ ታጣቂ የመንግስትን ሰዎች ትጥቅ የሚያስፈታበት ፣ አገሪቱ አሁን ላለችበት ቀውስ መናሃሪያ የሆነ ክልል ነው።

በአጠቃላይ ኦሮሚያ የሚባለው ክልል አናሳ ፍትህና የተትረፈረፈ አለመረጋጋት (A less just and more unstable region) የሆነና ይሄን መንግስት በህዝቡ እንድጠላ እያደረገ ያለ ክልል ነው።።

የአንድን ክልል ህዝብ የቧምቧ መስመሩ ብቻ በክልላቸው ስለሚያልፍ ውሃ ለስድስት ወራት መከልከል ምን ይባላል ? እረ ለመሆኑ ክልሉ እንደዚህ ስርአት አልባና ጋጠወጥ ሲሆን የክልሉ ፕሬዚደንት ለማ መገርሳ የማንን ጎፈሬ እያበጠረ ነው? ይሄ ኦሮሚያ የሚባል ክልል በዚህ የስርአት አልበኝነት መፈልፈያና መናሃሪያነቱ ከቀጠለ ለዚህ መንግስት መዳከምና መፈራረስ ብቸኛ ተጠያቂ መሆኑ አይቀርም።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.