Wednesday, April 8, 2020
Home > ዜና > ክላሊታንን የሚጎዱ 10 ልምዶች!

ክላሊታንን የሚጎዱ 10 ልምዶች!

1) ሽንትን መቋጠር

ሽንት ስይሸኑ ረጅም ግዜ መቆየት ኩላሊት ከሚጎዳባቸው ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ ይጠቀሳል። ሽንት በፊኛ ውስጥ ረጅም ሰአት ሲቆይ በውስጡ የሚያድጉት ባክቴሪያዎች ይበራከታሉ። እንዚህ ባክቴሪያዎች የሽንት ቧንቧ ወይም የኩላሊት ኢንፌክሽን ሊያመጡ ይችላሉ። ሽንትን መያዝ ኩላሊት ላይ በሚያደርሰው ጫናም ኩላሊት ተጎድቶ ሽንትን የመቆጣጠር ችሎታችንን ሊያጠፋ ይችላል። በየግዜው ሽንትዎን የሚይዙ ከሆነ በፍጥነት ልማዱን ማቆም አለብዎት። በስራ ምንም ያህል ቢጠመዱም የተፈጥሮ ጥሪን ሰምቶ ማስተናገድ ተገቢ ነው።

2) በቂ ውሃ አለመጠጣት

በቂ ውሃ አለመጠጣት ኩላሊት ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። የኩላሊት ዋና ስራ የሰውነታችንን ቆሻሻ ማስወጣት አና ኢሪትሮሳይት ማምረት ነው።

ሰውነታችን ውሃ ሲያንሰው ወደ እኩላሊታችን የሚሄደው የደም መጠን ይቀንሳል። ደማችን ይበልጥ ይረጋል። በዚህም ሁኔታ እኩላሊታችን ደማችን ውስጥ ያለውን ቆሻሻ ማጣራት ይቸገራል። ቆሻሻው በጨመረ ቁጥር ለጤናችን አደጋ ይሆናል። እንደ ናሽናል ኩላሊት ፋውንዴሽን አንድ ሰው በቀን ቢያንስ ከ10 እስከ 12 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት አለበት። ነገር ግን ውሃ ማብዛትም ለኩላሊት ህመም ሊፈጥር ይችላል። ስለዚህ ማብዛት የለብንም።

3) ጨው ና ስኳር ማብዛት

ብዙ ጨው መመገብ እኩላሊታችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያመጣ ይችላል። በምንመገበው ጨው የሚገኘውን ሶዲየም 95% ያህሉ በእኩላሊታችን ነው የሚቀየረው። ጨው ስናበዛ እኩላሊታችን ጨውን ለማጣራት ይበልጥ መስራት ይኖርበታል። እኩላሊቶቻችን ከአቅማቸው በላይ ሲሰሩ ሰውነታችን ውስጥ ከፍተኛ ውሃ ጥርቅም ይፈጠራል። ይህ ጥርቅም የደም ግፊታችንን ይጨምራል ለኩላሊት ህመምም ተጋላጭነታችንን ይጨምራል።

4) ፔይን ኪለር(ህመም የሚቀንሱ) መድሃኒቶችን መጠቀም ማዘውተር:: ብዙዎቻችን በየግዜው የሚሰማንን እራስ ምታት እና የህመም ስሜቶች ለማስታገስ ፔይን ኪለርን አዘውትረን እንጠቀማለን። እንደዚህ ስናደርግ ግን ሳናውቀው እኩላሊታችንን ጨምሮ የተለያዩ የሰውነት አክሎችን እየጎዳን ነው። የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ወደ ኩላሊት የሚሄደውን የደም ዝውውር መጠን ይቀንሳሉ። የኩላሊትን ስራ ይረብሻሉ። አልፎም በከፍተኛ ደረጃ መድሃኒቶቹን መጠቀም የሰገራ መቆጣጠር ብቃታችንን ያጠፋል። ክሮኒክ ኢተርስቲሻል ኔፍራይቲስ የሚባል ዘላቂ የኩላሊት ህመም ያስከትላል። የኩላሊት ህመም ካለብዎ ዶክተርዎን ሳያማክሩ የህመም ማደንዘዣ መድሃኒቶችን አይጠቀሙ። እኩላሊታችን ያለችግር እየሰራም ቢሆን መድሃኒቶቹን በትንሹ ነው መጠቀም ያለብን።

5) ፕሮቲን ያላቸው ምግቦች ማብዛት

ፕሮቲን ለሰውነታችን እና ለጤናችን አስፈላጊ የሆነ ንጥረ ነገር ነው። ግን ስጋ ወይም ሌላ ፕሮቲን ጠገብ ምግቦችን ከልክ በላይ የምንበላ ከሆነ እራሳችንን ለኩላሊት ህመም እያጋለጥን ነው።

የኩላሊት አንዱ ጥቅም ፕሮቲንን በመፍጨት ወደ ናይትሮጅን ቀይሮ ማስወገድ ነው። ከፍተኛ የፕሮቲን ተጠቃሚ ከሆንን እኩላሊታችን ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረግንበት ይሆናል። የኩላሊት ህመም ያለባቸው ሰዎች ቀይ ስጋ ከመብላት መቆጠብ ይኖርባቸዋል።

6) መጠጥ ማብዛት

መጠጥ ኩላሊታችን እና ጉበታችን ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል። በከፍተኛ ደረጃ መጠጣት ሪናል ቲዩቡልስ የሚባለው አካላችን ላይ የዩሪክ አሲድ ክምችት እንዲፈጠር ያደርጋል። ይህም የኩላሊት ስራ ማቆም ሊያስከትል ይችላል። አልኮል ሰውነታችን ላይ ውሃ ማነስ ስለሚፈጥር በዛ ረገድም ለእኩላሊታችን ጥሩ አይደለም።

7) ሺሻ ና ሲጋራ ማጬስ

እንደ ሴንተር ፎር ዲዚዝ ኮንትሮል(ሲዲሲ) ማጨስ ኩላሊትን ጨምሮ ለእያንዳንዱ የሰውነት አካል መጥፎ ነው። ብዙ ጥናቶች በማጨስ እና ኩላሊት በሽታ መሃከል ከፍተኛ ግንኙነት እንዳለ ይናገራሉ።

ኤንድ ስቴጅ ሪናል ዲዚዝ(ኢኤስአርዲ) ለሚባለው በሽታ ማጨስ እንደ አንደኛ መንስኤ ተጠቃሽ ነው። ማጨስ የደም ግፊትን እና የልብ ትርታን ይጨምራል። በሰውነታችን ውስጥ የደም ዝውውር ይቀንሳል። የኩላሊት በሽታ ካለብን ይበልጥ ያባብሰዋል።

8) ከመጠን በላይ ቡና መጠጣት

ቡናን ማብዛት የደም ግፊትን ይጨምራል። እሱ ደግሞ በተራው እኩላሊታችን ላይ ጫና ይፈጥራል። ከግዜ በኋላ እኩላሊታችን እየተጎዳ ይመጣል።

በ2002 በኩላሊት ኢንተርናሽናል እንደታተመው ጥናት ቡና መጠጣት ከኩላሊት ጠጠር ጋር ግንኙነት አለው።

ቡናን በመጠኑ መጠጣት ለአብዛኛው ሰው ችግር አያመጣም። በቀን ከ 1 እስክ ሁለት ስኒ ቡና እና 3 ስኒ ሻይ መጠጣት ችግር አያመጣም።

9) ቀላል ኢንፌክሽኖችን በግዜው አለመከታተል

ጉንፋን፣ ቶንሲል እና ለመሳሰሉት ቀላል ኢንፌክሽኖች ተገቢውን ክትትል አለማግኘት ኩላሊትን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል።

ብዙ የኩላሊት ህመም ያላቸው ሰዎች ሌላ ህመም ሲያማቸው ባለማረፍ ይታወቃሉ። በተጨማሪም የኩላሊት ህመም ያለባቸው ሰዎች በአየር ጸባይ ለውጥ በቀላሉ ይታመማሉ። ቀላል ህመም የሚፈጥሩ ባክቴሪያዎች እና ቫይርሶች ኩላሊት ላይ ጉዳት ይፈጥራሉ። እነዚህን ቀላል ህመሞች ተከታትሎ መፍትሄ መፍጠር ያስፈልጋል።

10) የእንቅልፍ እጦት

በስራ መጠመድ ምክንያት ብዙ ሰዎች የእንቅልፍን አስፈላጊነት ይረሳሉ። ከ6-8 ሰአት መተኛት ለጤናችን አስፈላጊ ነገር ነው። በእንቅልፍ ግዜ የተጎዱ የሰውነት አካላችን ይታደሳሉ። በቂ እንቅልፍ አለማግኘት ይህ እድሳት በተገቢው ሁኔት እንዳይካሄድ እንቅፋት ይሆናል። ኩላሊት እና ሌሎች የሰውነታችን አካሎች ይጎዳሉ።

ሌሎች ጥናቶች እንደሚጠቁሙት እንቅልፍ እጦት የደም ግፊትን ይጨምራል። ይህም ለኩላሊት መጥፎ ነገር ነው።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.