Sunday, April 5, 2020
Home > ዜና > በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ የሚመራ ልዑካን ወደውጭ አቀና – FBC

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ የሚመራ ልዑካን ወደውጭ አቀና – FBC

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው ልዑክ ወደ ሳዑዲ ያቀናው   ከጥቅምት 13 እስከ 15 በሚካሄደው  የኢንቨስትመንት ፎረም ለማሰታፍ ነው ተብሏል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው ልዑክ ወደ ሳዑዲ ያቀናው   ከጥቅምት 13 እስከ 15 በሚካሄደው  የኢንቨስትመንት ፎረም ለማሰታፍ ነው ተብሏል።

የኢንቨስትመንት ፎረሙ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ አፍሪካን በመወከል፥ የአህጉሪቱን እምቅ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና መፃዒ ዕድሎችን በተመለከተ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስተዋወቅ እና አለም አቀፍ ባለሃብቶችን ለመሳብ የሚያግዙ መልዕክቶችን እንደሚያስተላልፉ ተነግሯል።

ከፎረሙ ጎን ለጎን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሳዑዲ ዓረቢያ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን በፎረሙ ለመሳተፍ ለሊት ሪያድ ሲገቡ የሳውድ አረቢያ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በክብር ተቀብለዋቸዋል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.