Sunday, April 5, 2020
Home > ዜና > በአሚሪካ ኢንዲያናፖሊስ ግዛት ዙሪ የተባለች እንስት አንበሳ የሦስት ልጆቿ አባት ላይ እርምጃ ወሰደች! – BBC NEWS

በአሚሪካ ኢንዲያናፖሊስ ግዛት ዙሪ የተባለች እንስት አንበሳ የሦስት ልጆቿ አባት ላይ እርምጃ ወሰደች! – BBC NEWS

ዙሪ የምትሰኘውና በነፍስ ግድያ የተጠረጠረችው 10 ዓመቷ ሲሆን የልጆቿ አባት ኒያክ ደግሞ የ10 ዓመት ጎረምሳ ነው። ከመሞቱ በፊት የመካነ አራዊቱ ባለስልጣናት ሊለያይዋቸው ባለመቻላቸው ታፍኖ መሞቱ ተዘግቧል።

እነዚህ ሁለት አንበሶች በአንድ ጣሪያ ስር ለስምንት ዓመታት አብረው በፍቅር የኖሩ ሲሆን እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም 3 ደቦሎችን አፍርተዋል።

የመካነ አራዊቱ ባልደረቦች በድርጅቱ ፌስቡክ ገፅ ላይ እንዳስቀመጡት በትክክል ምን እንደተፈጠረ “ጥልቅ ምርመራ” እናካሂዳለን ብለዋል።

“ኒያክ ግርማ ሞገሱ የሚያስደምም አንበሳ ነበር፤ በእጅጉ ሞቱ ልብ ሰባሪ ነው” ሲሉም አክለዋል።

የመካነ አራዊቱ ሰራተኞች ባልተለመደ መልኩ ከአናብስቱ መኖሪያ ማጓራት መስማታቸውንና በፍጥነት ወደስፍራው ማምራታቸውን ያስታውሳሉ።

ሲደርሱም ዙሪ የኒያክን አንገት ጨምድዳ ይዛ የነበረ ሲሆን ሊያስለቅቋት በሞከሩ ቁጥር መንቀሳቀስ እስኪያቆም ድረስ ሳትለቀው መቆየቷን ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት በሁለቱ መካከል እንዲህ ኃይል የተቀላቀለበት ተግባር አስተውለው እንደማያውቁ የተናገሩት ሰራተኞቹ ” ከአንበሳው ጋር የተለየ ቅርበት ነበረን፤ በሞቱ እጅጉን አዝነናል” ብለዋል።

የኢንዲያና ፖሊስ መካነ አራዊት ሃላፊ በበኩሉ “ለበርካቶቻችን እንደቤተሰብ ነበር” በማለት በመካነ አራዊቱ የሚገኙ አንበሶች አኗኗር ላይ ምንም አይነት ነገር ለመቀየር እቅድ እንደሌለ ጨምረው ገልፀዋል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.