Sunday, April 5, 2020
Home > ዜና > አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ የመጀመርያዋ ሴት የኢትዮጵያ ኘሬዝዳንት ሆነው ዛሬ ቃለመሃላ ይፈፅማሉ!

አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ የመጀመርያዋ ሴት የኢትዮጵያ ኘሬዝዳንት ሆነው ዛሬ ቃለመሃላ ይፈፅማሉ!

አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴዛሬ ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ.ም በዶክተር ሙላቱ ተሾመ ቦታ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆኖው ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክርቤቶች በጋራ ዛሬ በሚያደርጋቸው አስቸኳይ ጉባኤዎች ላይ የስራ ጊዜያቸው ሊጠናቀቅ አንድ ዓመት የቀራቸውን ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የመልቀቂያ ደብዳቤ ተቀብሎ በማጽደቅ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋን ሴት ኘሬዝዳንት ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል።

አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በኢጋድ በኃላም በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን፣ በዩኔስኮ የኢትዮጵያ ተወካይ፣ በቱኒዝያና በሞሮኮ በአምባሳደርነት አገራቸውን አገልግለዋል።

በተባበሩት መንግስታት ስር የነበረው የተቀናጀው የሰላም አስከባሪ ኃይል ተወካይ በመሆን በሴንትራል አፍሪካ ሰርተዋል። በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንና በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነዉም አገልግለዋል። በኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር በመሆንም የመሪነት ችሎታቸው አስመስክረዋል።

በቀድሞ የተመድ ሊቀመንበር ባንኪ ሙን አጪነትና በመለስ ዜናዊ ሙሉ ድጋፍ ሰጪነት የተባበሩት መንግስታት የናይሮቢ ኦፊስ ዳይሬክተር ጀነራል ለመሆን የበቁ በአንደር ሴክረተሪ ጄኔራል ማዕረግ ቦታዉን የያዙ የመጀመርያ እንስት ናቸው። ባንኪ ሙን ለቀው አንቶኞ ጉተሬዝ ሲተኩም አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘዉዴ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ህብረት ልዩ መልእክተኛ አድርገው ሾሟቸዋል።

የፈረንሳዩ ሞንተፔለ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ የሆኑት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ የመጀመርያ ሴት ፕሬዚደንት ሆነው በዛሬው ዕለት ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.