Wednesday, April 8, 2020
Home > ዜና > “የውል ስምምነቱን የፈረምኩት በአቶ መለስ ትእዛዝ ነው” አቶ አባይ ፀሃዬ

“የውል ስምምነቱን የፈረምኩት በአቶ መለስ ትእዛዝ ነው” አቶ አባይ ፀሃዬ

አቶ ዓባይ ጸሐየ ከሰሞኑን ከአንድ የመገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ በሳቸው ዙሪያ ስለሚነሱ አስተያቶች ምላሽ ሰጥተዋል ፡፡ ከሱዳን የመሬት ውዝግብ እስከ ስኳር ኮርፖሬሽን ዝርፊያ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ብጥብጥ እሰከ ግል የሀብት መጠናቸው ድረስ ያሉ ጉዳዮችንም ሲያብራሩ ተስተውለዋል፡፡

ከህወሓት ሊህቃን መካካል አንዱ የሆኑት አቶ ዓባይ ጥያቄዎች የሚያስደነብሯቸው አይነት ሰው አይመስሉም፡፡ በዚህ የተነሳም የሚቀርቡ ሃሳቦችን ተረጋግተው ለመመልስ ሞክረዋል፡፡ መልሶቻቸው ግን ከሞላ ጎደል ነገርን ከራሳቸው ላይ ለማራቅ የሚጥሩ ናቸው፡፡

ለብዙ ውድቀቶች መነሻውን ከራሳቸው ይልቅ የመንግትን አቅጣጫ የሚያደርጉትም ለዚህ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ምለሽ በእሳቸው ደረጃ ለነበረ የፓርቲው አድራጊ ፈጣሪ ሰው ብዙ የሚያዋጣ አይደለም፡፡

አቶ ዓባይ ለረጅም ጊዜ የተብጠለጠሉበትን የሱዳን መሬት ጉዳይ በአግባቡ እየመለሱትም እራሱ ሰበብ ሲፈልጉለት ይታያሉ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ በቅርቡ ለፓርላማው ካብራሩት ሀሳብ ጋር ኩታ ገጠም የሆነው የአቶ አባይ መከራከሪያ ለሱዳን የተሰጠ መሬት አለመኖሩን አስረግጦ ተናግሯል፡፡ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የሚታየው የእሳቸው ፊርማ ያረፈበት የውል ስምምነት ሰነድም ለድንበር ማካልል የተፈረመ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

አቶ ዓባይ የእኔ ፊርማ ያለበት ይህ የውል ስምምነት ሁለቱ ሀገራት የጋራ የድንበር ኮሚሽን አቋቁመው ድንበር እስኪያካልሉ ድረስ በጠረፍ አከባቢ ያለው ህዘብ ባለበት ቦታ እንዲቆይ የሚስችልና ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ያደረገ የመግባቢያ ውል ነው ብለዋል፡፡ የቀድሞው ታዋቂ ፖለቲከኛ እንዲህ ያለ ምላሽ ግን እዚህ ቦታ ላይም ከሰበብ አላመለጠም፡፡ ይህን ውል የተፈራራምኩት ሳላውቅ በአቶ መለስ ትዕዛዝ ነው ሲሉ የሚደመጡትም ለዚህ ነው፡፡ አቶ ዓባይ ከላይ ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ያደረገ የመገባቢያ ሰነድ ነው ይሉንና ከታች ሳላውቅ በአቶ መለስ ትዕዛዝ ነው የፈረምኩት የሚል ተቃርኖ ያለበት አስተያት ይሰነዝራሉ፡፡

በእኔ ግምት ይህ ዓይነቱ ተቃርኖ የሚሰተዋልበት መልሽ የጉምቱው ፖለቲከኛ ስነልቦና ችግር እንደገጠመው የሚያሳይ ነው፡፡ ሰነፍ ተማሪ የሚያውቀውን ጥያቄ ብትጠይቀውም ምላሹን ከጎበዝ ተማሪ ላይ ካላረጋገጥ የመለሰ አይመስለውም የሚለውም ብሂል እዚህ ቦታ ላይ የሚሰራ ይመስለኛል፡፡ ሀገርን ተጠቃሚ ያደረገ የመግባቢያ ሰንድ ፈረምኩ ያሉን አቶ ዓባይ የአቶ መለስን ስም ከዚህ ስምምነት ጋር ለማስተሳሰር መሞከራቸው ፖለቲካችን ከቤተ-መንግሰት አልፎ መንግሰት ሰማይ ደረስ መዝለቁን ያስታውሰናል፡፡

እንዲህ ያለው ፖለተካችን ሰማይ ቤት ድርስ የመውሰድ አባዜ ግን በአቶ ዓባይ የተጀመረ አይደልም፡፡ አቶ ልደቱም በቅርቡ ኢህአዴግ እንድሆን አቶ መለስ ይፈልጉ ነበር ብለው ደረሰኝ የሌለው ማወራረጃ ጀባ ብለውናል፡፡ አሜሪካን ሀገር ያሉ አብያተ ክርስትያናት የጎንደር፣ የጎጃም የኦሮሞ፣ የትግራይ መባላቸውን የተመለከቱት መረራ ጉዲናም (ዶ/ር) ፖለቲካችን መሬት አልበቃው ብሎ ሰማይ ቤት ደርሷል ያሉት ለዚህ ነበር፡፡ ይህ ዓይነቱን ፖለቲካን ሰማይ ቤት ድረስ የመውሰድ ድርጊት ከዚህ ቀደም በዲያስፖራው ሲፈጸም የኖረ ቢሆንም ዛሬ ታላላቆች ፖለቲከኞቻችንም ተቀላቅለውታል፡፡ ይህ ደግሞ ነገርን ከራስ ለመግፋት ካልሆነ ትርፍ የሚያስገኝ አይደለም፡፡

በተሾመ ታደደ አትዮ ኒውስ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.