Sunday, April 5, 2020
Home > ዜና > በጣም አሳዛኝ ዜና የ18 ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ

በጣም አሳዛኝ ዜና የ18 ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ

በዮርዳኖስ ድንገተኛ ጎርፍ የ18 ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ

በዮርዳኖስ በደረሰ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ 18 ሰዎች ህይወታቸዉን አጡ፡፡

ሟቾቹ አደገኛ በሆነዉ ሙት ባህር አቅራቢያ የነበሩ ተማሪዎችና መምህራን ናቸዉ ተብሏል፡፡

አብዛኞቹም ከ 14 አመት በታች መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር ሮይተርስን ጠቅሶ እንደዘገበዉ 34 ሰዎች አሁንም በጎርፉ አደጋ ዉስጥ በመሆናቸዉ የአደጋ ሰራተኞች ና የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ጭምር በሂሊኮፕተር በመታገዝ ህይወት ለማዳን እየጣሩ ነዉ፡፡

በአደጋዉ ቁጥራቸዉ እስካሁን ያልታወቁ ሰዎችም አደጋዉ በደረሰበት አቅራብያ በሚገኝ ሾሁና የተባለ ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸዉ ነዉ ተብሏል፡፡

አደጋዉ በድንገት ያለወቅቱ በዘነበ ከባድ ዝናብ ሳቢያ የደረሰ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ምንጭ፦ሚድል ኢስት ሞኒተር

ሼር ያድርጉት

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.