Sunday, April 5, 2020
Home > ዜና > ጣና ለይ የተከሰተው እምቦጭ አረም ቀንሷል እየተባለ ነው

ጣና ለይ የተከሰተው እምቦጭ አረም ቀንሷል እየተባለ ነው

መቼም በአሁን ሰዓት መነጋገሪያችን አንድ ጉዳይ አለ እሱም ጣና እና ጣና ነው


በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተው የእምቦጭ አረም ካለፈው ዓመት አንፃር ሲታይ መቀነሱን የክልሉ መንግስት ገለፀ

በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተው የእምቦጭ አረም ካለፈው ዓመት አንፃር ሲታይ መቀነሱን የአማራ ክልል የአካባቢ ደን እና ዱር እንስሳት ልማት ጥበቃ ባለስልጣን ገለፀ።

የባለስልጣኑ ዳይሬክተር ዶክተር በላይነህ አየለ እንደተናገሩት፥በጣና ሃይቅ ላይ የተከሰተው እምቦጭ አረም በሚገኝባቸው ስድስት ወረዳዎች እና 20 ቀበሌዎች ላይ ሙያተኞች ባደረጉት የልኬት ጥናት መሰረት አረሙ ካለፈው አመት አንፃር መቀኑሱ ተረጋግጧል።

አረሙን በመከላከል ሂደትም በከተሞች አካባቢ የተቀዛቀዘ ቢሆንም አርሶ አደሩ እንቅስቃሴውን የበለጠ አጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል።

ጥቅምት እና ህዳር ወራት አረሙ የሚያብብበት እና የሚራባበበት ወቅት በመሆኑም በዚህ ወቅት የማንኛውም ማህበረሰብ ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን ዶክተር በላይነህ አስረድተዋል።

ምንጭ፦ኤፍ.ቢ.ሲ

ሼርርርርርርር

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.