Sunday, April 5, 2020
Home > ጠቃሚ መረጃዎች > ፌስቡክ ትልቅና ጠቃሚ ስራ ሰራ!

ፌስቡክ ትልቅና ጠቃሚ ስራ ሰራ!

ፌስቡክ ትልቅና ጠቃሚ ስራ ሰራ!
ፌስቡክ በሦስት ወራት ብቻ 8.7 ሚሊዮን እርቃናቸውን የሚታዩ የሕጻናትን ምስል አስወገደ፡፡

ማኅበራዊ የመገናኛ መረቡ እንዳታስታወቀው ሕጻናትን የተመለከቱ ጾታዊ ግንኙነት ቀስቃሽ ምስሎችን እንደተለቀቁ ማስወገድ የሚችል አዲስ ‹‹ሶፍትዌር›› ተፈጥሯል፡፡

ሶፍትዌሩ አገልግሎት ላይ የዋለው ባለፈው ዓመት ቢሆንም ለሕዝብ ይፋ የሆነው በቅርቡ ነው፡፡

እንደ ፌስቡክ ገለጻ አዲሱ ሶፍትዌር ከሕጻናት ጋር የተያያዙ የፆታዊ ትንኮሳዎችን የሚያሳዩ መረጃዎችን ማወቅ የሚችል ነው፡፡

እንዲወገዱ ከተደረጉት ስምንት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ምስሎች ውስጥ 99 በመቶ ያህሉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከመድረሳቸው በፊት እንዲወገዱ ተደርገዋል፡፡

ፌስቡክ የጥላቻና የዘረኝነት ቅስቀሳ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶችም የሚያስወግድ አሠራር እንደሚዘረጋ አስታውቆ ነበር፡፡

በሌላ በኩል ፌስቡክ ከመረጃ ማሹለክ ቅሌት ጋር በተያያዘ 500 ሺህ ፓውንድ ተቀጥቷል፡፡

ቅጣቱ የተላለፈበት ለኮምፒዩተር መተግበሪያ ባለሙያዎች የግለሰቦችን ሚስጥር እንዲበረብሩ መፍቀዱን ተከትሎ ነው፡፡

ለቅጣት የዳረጉትም የእንግሊዝ የመረጃ ደህንነት ጠበቆች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ ነው

ሼር በማድረግ ይህን ጠቃሚ ሀሳብ ለጓደኛዎ ያጋሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.