Wednesday, January 22, 2020
Home > ዜና > በተለያዩ ከተሞች የተካሄዱ ሰልፎች አስገራሚ ክስተት ታየባቸው

በተለያዩ ከተሞች የተካሄዱ ሰልፎች አስገራሚ ክስተት ታየባቸው

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የተካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎች በሰላም ተጠናቅቀዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፎቹ በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ደብረ ታቦር ፣ ወልድያ፣ ደብረ ብርሃን፣ ሰቆጣ፣ ደሴ፣ ላልይበላ … ከተሞች ነበር የተካሄዱት፡፡

በሰልፎቹ ላይ ለላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትና ለጣና ሐይቅ ደኅንነት ትኩረት እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡

ከመልዕክቶቹ ከፊሎቹን እናስታውሳችሁ፡፡
•ባንሠራ የታሪክ ተወቃሽ አንሁን! ላልይበላን እንታደግ! ባሕር ዳር

•የአፋር ደም የአማራ ደም ነው! ፍትሕ ለአፋር!ባሕር ዳር

•የራያ ወንድሞቻችን ላይ የሚፈጸመው ግድያና አፈና ይቁም ደብረ ብርሃን
•የራያ ወንድሞቻችን ላይ የሚፈጸመው ግድያና አፈና ይቁም! ደብረ ብርሃን

•የጣና፣ ላልይበላ፣ ራያ፣ ወልቃት፣ መተከል፣ ሸዋ ጉዳይ በአስቸኳይ እልባት ያግኝ! ደብረ ብርሃን
•ወንድሞቻችን የሞቱለትን ክቡር ዓላማ ዳር እናደርሳለን ወልድያ
•የራያና የወልቃት የማንነት ጥያቄዎች ሊመለሱ ይገባል! ወልድያ

•የራያ ሕጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ይማሩ! ወልድያ
•በራያ እና ወልቃይት እየተፈጸመ ያለው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ይቁም! ወልድያ
•ላልይበላ በኛ ጊዜ አይፈርስም፤ ጣና በኛ ጊዜ አይደርቅም! ወልድያ

•የፌዴራል መንግሥት ለጥያቄዎች ምላሽ ሊሰጥ ይገባል!ወልድያ
•ማንነት ከመብቶች ሁሉ የበላይ መብት ነው! ፍትሕ ለሰዎች!ሰቆጣ

•መንግሥት ላልይበላንና ጣናን አለመታደጉ ተጠያቂነት ብቻ ሳይሆን በታሪክም ተወቃሽ ያደርጋል! ሰቆጣ
•በማንነት መፈናቀልና መሞት ይቁም! ሰቆጣ
•መንግሥት በሁለቱ ክልሎች ገብቶ መፍትሔ እንዲሰጥ እንጠይቃለን!ሰቆጣ

•ሁሉም ኢትዮጵያዊ በየትናውም የኢትዮጵያ ክፍል የመኖር፣ የመሥራት፣ የመንቀሳቀስ መብቱ ይከበር! ሰቆጣ
•ፍትሕ ለአክሱም ሙስሊሞች ጎንደር

•ላልይበላ የኢትዮጵያ በመሆኑ ልንጠብቀው ይገባል! ጎንደር
•የጣናን ጉዳይ በቸልታ ማዬት አማራን ከማጥፋት አይተናነስም! ጎንደር
የአማራ ሕዝብ የግዛትና የሕዝብ አንድነት ይከበር!
ጎንደር

•ወልቃይት፣ ራያ፣ ጸለምትና መተከል ወደ ቀደመ ርስታቸው ይመለሱ! ጎንደር
•ላልይበላ፣ ፋሲልና ጣና ቅርስ ብቻ ሳይሆኑ ትናንትን የምናይባቸው ዓይኖቻችን፣ ዛሬን የምንኖርባቸው ኩራታችን ናቸው! ጎንደር

•ቅማንትም አማራም አንድ ነው! ጎንደር
•ማንነት በዘመን ብዛት አይለወጥም፤ ራያ ወሎ ነው፤ ወሎም አማራ ነው! ጎንደር
•ዶር ዐብይና አስተዳደሩ የአማራን ሕዝብ እንባ እንዴት ማድረቅ ተሳናችሁ? ጎንደር

•ለላሊበላ ፣ፋሲል እና ጣና ትኩረት ይሰጥ፤የወልቃይትና ራያ የማንነት ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል፤ቅርስ እየፈረሰ ታሪክ አይሰራም፡፡ደብረ ታቦር

ምንጭ፦አብመድ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.