Monday, May 25, 2020
Home > ዜና > ጠቅላይ ሚኒስተራችን ስለመከላከያ አስገራሚ ንግግ ተናገሩ

ጠቅላይ ሚኒስተራችን ስለመከላከያ አስገራሚ ንግግ ተናገሩ

በመከላከያ ሰራዊት በየደረጃው እየተደረገ የነበረው፡ውይይትን ለማጠቃለል በዛሬው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከክፍለ ጦር አዛዦች በላይካሉ ወታደራዊ፡አመራሮች ጋር በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር እብይ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ መከላከያ ሰራዊትን በሁሉም መስክ ብቁ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት በከፍተኛ ግለት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

ይህም ከለውጡ ጊዜ ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው ዘርፉን ዘመናዊ፣ ብቁ እና ውጤታማ ለማድረግ የሚከናወን ጥረት አካል ሲሆን፥ በቅርቡ በውስን ወታደሮች የተከሰተው ከወታደራዊ ዲሲፕሊን ያፈነገጠ ድርጊትም እንደ መነሻ ተወድሷል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በዛሬው ገለፃቸውበዋነኝነት በመከላከያ አመራር ልቀት ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ በተለይም የመከላከያ ልቀትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የአመራር ክህሎቶች፣ የግዳጅ አፈፃፀም ሂደት ላይ ሃይልና ስልጣንን በተገቢው መጠን፣ በአግባብ ሁኔታ በመጠቀም ቅቡልነት ማግኘት የሚቻልበት መንገድ ላይ ውይይት አድርገዋል።

መከላከያ ሰራዊት በአንዲት ሀገር የሚኖር ብቸኛው የታጠቀ አካል በመሆኑ ይህንን ሃላፊነት በህገ መንግስታዊ መልኩ መወጣቱ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ እንደሆነም ነው በማብራሪያቸው ላይ ያነሱት።

በህገ መንግስቱ አንቀጽ 87/4 መሰረት “መከላከያ በማንኛውም ጊዜ ለህገ መንግስቱ ተገዢ ይሆናል” በሚል በተለየ አፅንኦት መከላከያን ከህገ መንግስታዊ ስርዓት ጠባቂነትና ተገዢነት ጋር አቆራኝቶታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ላይ የምታፈሰው በጀትና የምትሰጠው ትኩረትም ይህንን ቃል ኪዳን መሰረት ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

በህገ መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ለግዳጅ ሲሰማራ በታጠቀው መሳሪያ ምክንያት ሀይል ቢኖረውም እርምጃው ቅቡልነትን በሚያረጋግጥ መልኩ በከፍተኛ፡ጥንቃቄ የህግ ተገዥነትና የህዝብ ተቆርቋሪነት ስሜት ማከናወን እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፅዕኖት ተናግረዋል።

ይህንንም ለማረጋገጥ የግዳጅ አፈፃፀም መመሪያዎች እንደሚከለሱና በመመሪያው መሰረት ጥብቅ የእዝና፡የቁጥጥር ስርዓት በማስፈን መስራት አስፈላጊ እንደሆነ ነው የገለፁት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መከላከያ ሰራዊት ሀይል አለኝ ብሎ እርምጃ የማይወስድ ቢሆንም ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመጠበቅ ግን በተሰጠው ስልጣን በጥብቅ መመሪያ፡የተቃኘ ሰላም ወዳድ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ይሁንታ የሚሰጡት ተግባራዊ መፍትሄ መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ባለፉት ሶስት ወራት መከላከያ በለውጥ ጎዳና ላይ ይገኛል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ለውጡም በህጋዊ ማዕቀፈች፣ በአደረጃጀት፣ በመፈፀም ብቃት እና በትጥቅ እንደሚገለፅ አመልክተዋል።

በህጋዊ ማእቀፍ ረገድም መከላከያ ሰራዊት መቋቋሚያ አዋጅ የባህር ሀይል አደረጃጀትን አካቶ እንዲሁም ወደፊት የሳይበርና የህዋ/ስፔስ/ ምህዳሮችን ለማካተት በሚያስችል መልኩ መሻሻሉ ነው የተጠቆሙት።

በዚህም ዘመናዊው ዓውደ ውጊያ በሚጠይቃቸው አምስቱም ምህዳሮች ማለትም የምድር፣ ዓየር፣ ባህር፣ ሳይበርና ህዋ ዝግጁ የሆነ መከላከያ ሰራዊት የመገንባት ሂደት መጀመሩ አስታውቀዋል።የአሰራር መመሪያዎች እንዲዳብሩና ዘመናዊ ሰራዊት ሊኖረው በሚገባው ደረጃ እንዲሆኑ ከፍተኛ ጥረት መደረጉንም ነው ያነሱት።

የሀገሪቱ አቅም በፈቀደ መጠን ቴክኖሎጂን የሚታጠቅ፣ በራሱ አቅም መጠገን፣ ማሳደግ ብሎም መፍጠር የሚችል እንዲሆን በርካታ የአቅም ግንባታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቆመው፥ መከላከያ ከቴክኖሎጂ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለውና እንደ ሌሎች ሀገራት ከራሱ አልፎ ለሌሎች ዘርፎች ምንጭ መሆን የሚችል የቴክኖሎጂ ማእከል እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

መከላከያ ሰራዊቱ በሁሉም ደረጃዎች በህገመንግስቱ እንደተቀመጠው የሁሉንም ብሄር ብሄረሰቦች ተዋፅኦ የጠበቀ ለማድረግ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ተናግረዋል።

በአደረጃጀት በኩልም ከዚህ በፊት የነበረው አደረጃጀት በርካታ ማነቆዎች የነበሩት፣ የሲቪልና መከላከያ ቅንብርን በሚገባው ደረጃ ያላካተተ በመሆኑ ሰፊ ጥናት ተደርጎ አዲስ አደረጃጀት መፅደቁን ነው የገለፁት።

የፋይናንስ አጠቃቀምና አወጣጥ ስርዓት ዘርፉ የሚጠይቀው ሚስጥራዊነት እንደተጠበቀ ሆኖ በግልፅ መመሪያዎች እንዲመራ የሚያስችል አሰራር ተዘርግቷልም ብለዋል።

መከላከያ በዘመናዊ ትጥቅ እንዲደራጅና ግዳጅ የመፈፀም ብቃቱ ከፍተኛ እንዲሆን የሚያስችሉ የተጠኑ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ መግለፃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያወጣው መግለጫ ያመለክታል።

ምንጭ፦ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.