Sunday, April 5, 2020
Home > ዜና > የኢምፔሪያል እና ሪቬራ ሆቴሎች የ 200 ሚሊዮን ብር የግዢ ድራማዎች በሸገር ታይምስ መጽሄት እንደተዘገበው!

የኢምፔሪያል እና ሪቬራ ሆቴሎች የ 200 ሚሊዮን ብር የግዢ ድራማዎች በሸገር ታይምስ መጽሄት እንደተዘገበው!

ሜቴክ በ 2004 ዓ/ም በአዲስ አበባ በተለምዶ ገርጂ ማዞሪያ ወይም ቦብ ማርሌ አደባባይ ላይ የተገነባውን ታዋቂውን ኢምፔሪያል ሆቴልን የገዛበት መንገድ እጅግ አነጋጋሪ ነው፡፡ ጉዳዩ ከፍተኛ ገንዘብ የወጣበት ብቻ ሳይሆን የግዢ ሂደት ደንቦችና መመሪያዎችን ያልተከተለ እንዲሁም ሙስና መፈጸሙን ብዙ ጠቋሚ ምልክቶች የታየበት ነበር፡፡

ጥር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ላይ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር የሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ዋና ጸሀፊ የነበረች ግለሰብ አንድ ደብዳቤ ለአለቃዋ ታቀርባለች፡፡ ጉዳዩ ለእንግዶች ማረፊያ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ተብሎ በጸሀፊዋ የቀረበው ደብዳቤ በግርጌው ላይ በዋና ዳይሬክተሩ በሜጀር ጀነራል ክንፈ ይፈጸም ተብሎ ወዲያው ተመራበት፡፡

የዚህን ደብዳቤ ምሪ ተከትሎም ደብዳቤው ከመቅረቡ በፊት ጥቅምት 7/2004 ዓ/ም የተቋቋመ አራት አባላት ያሉት አንድ የግዢ ኮሚቴ ለማስፈጸሙ ስራ ተሰየመ፡፡ ምቹ የእንግዳ ማረፊያ ቦታ ይመቻች የሚለውን ጥያቄ ያቀረቡት ጸሀፊም በዚህ ኮሚቴ ውስጥ ተካተው ነበር፡፡ ኮሚቴው ለእንግዶች ምቹ ማረፊያ ቦታ ማግኘቱንና እርሱም ኢምፔሪያል ሆቴል መሆኑን ጠቅሶ ግዢውን በድርድር ለመፈጸም ተፈቀደለት፡፡

በዋና ዳይሬክተሩ ይሁንታን ያገኘው አራት ሰዎችን የያዘው የግዢ ቡድን ከኢምፔሪያል ሆቴል ባለቤት ከሆነው ከአክሰስ ሪል ስቴት ጋር ቀጥታ ድርድር ጀመረ፡፡ በ 75 ሚሊዮን ብር ኢምቤሪያል ሆቴልን ለመግዛት ከአክሰስ ሪል ስቴት ጋር በድርድር ውል የተስማማው ሜቴክ ልክ ውሉ እንደተፈጸመ 24 ሚሊዮን 200 ሺህ ብር ከፈለ፡፡ ቀሪውን ሙሉ ክፍያም በ 9 ወራት ከፍሎ ለመጨረስ ተስማምቶም ነበር፡፡ በዚህ ውል መሰረት ሻጩ (አክሰስ ሪል ስቴት) የሸጠውን ኢምፔሪያል ሆቴል አድሶ ለገዢው ሜቴክ እንደሚያስረክብ ተስማምቶ ነበር፡፡

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.