Wednesday, January 22, 2020
Home > ዜና > በውስጥዎ ስንት አስደናቂ ነገር እንዳለ ያውቃሉ ?

በውስጥዎ ስንት አስደናቂ ነገር እንዳለ ያውቃሉ ?

በውስጥዎ ስንት አስደናቂ ነገር አለ!
እያንዳንዱ ሰው በቀን 2 ሊትር ምራቅ ያመርታል
በየደቂቃው ከ30ሺ – 40ሺ የቆዳ ሴሎች ይሞታሉ
ዓይኖቻችን በየዕለቱ 15ሺ ያህል ጊዜ ይርገበገባሉ
ከተፀነስንበት ሴኮንድ ጀምሮ፣ በሕይወትና በጤንነት
የምንንቀሳቀሰው ቅንጣት ታህል ስህተት ሳይፈፅሙ
ተግባራቸውን ስለሚፈፅሙ ነው፡፡
እስቲ ጥቂቱን እንይ፡፡ 20ሺህ ያህል ሀሳቦች በአንጎላችን
ውስጥ ምን ያህል የነርቭ ሴሎች እንዳሉ ያውቃሉ?
እጅግ በርካታ ናቸው-እስቲ ይገምቱ፡፡ በአንድ ሴኮንድ
ውስጥ በአማካይ ከአምስት እስከ 50 ጊዜ እርስ በርስ
መልእክት ይለዋወጣሉ፡፡ የነርቭ ሴሎች
የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች በቀን ከ10ሺ ኪ.ሜ
በላይ ይጓዛሉ፡፡ ከአዲስ አበባ አስመራ ድረስ አምስት
ጊዜ እንደመመላለስ ነው፡፡ የነርቭ ሴሎቹ ቁጥር ከመቶ
ቢሊዮን በላይ ነው፤ የፀጉር ያህል ውፍረት የላቸውም፡፡
በመሃላቸው ያለው ርቀትም እንደዚያው ኢምንት ነው፡፡
ነገር ግን ከብዛታቸውና በየሴኮንዱ ከሚለዋወጡት
የመልእክት ብዛት የተነሳ ተዓምር ይፈጥራሉ፡፡ አንድ ነገር
አይተው ወዲያውኑ “ይሄ ውሻ ነው፣ እንዳይነክሰኝ!”
“ብርቱካን ነው፣ ይጣፍጣል” “ሰው ነው፤ ዝነኛው
ሯጭነቱ ይደነቃል” “አንበሳ ነው፣ የጀግንነት ምሳሌ
ተደርጎ ይቆጠራል” … ለማለት የሚችሉት በዚህ ፍጥነት
ነው፡፡ በእነዚህ ነርቮች ነው እንግዲህ በቀን፣ 20ሺህ
ያህል ጊዜ የምናስበው።
እንደ በረዶ እንዳንቀዘቅዝ፣ እንደ ውሃ እንዳንፈላ
የሰውነታችን “አውቶማቲክ” እንቅስቃሴዎችንና ሂደቶችን
የሚቆጣጣረው hypothalamus የተባለው የአንጎል
ክፍል ነው፡፡ የሰውነታችን የሙቀትና የቅዝቃዜ መጠን
ከልክ እንዳያልፍም ይቆጣጠራል፡፡ በአንዳች ውጫዊ
ወይም ውስጣዊ ምክንያት የግማሽ ዲግሪ ሴንቲግሬድ
ለውጥ ከተፈጠረ፤ ሰውነታችን ሕይወት አድን የሙቀት
መጠን ማስተካከያ ያከናውናል፡፡
የሰውነታችን ሙቀት በጣም ከፍ ሲል፣ በቆዳችን ውስጥ
ያሉ የደም ስሮች ይሰፉና ሙቀት ያስወጣሉ፡፡ ቅዝቃዜ
ሲከሰት ደግሞ የደም ስሮች ጠበብ ይላሉ፤ ላብ
አመንጪ ዕጢዎችም ይዘጋሉ፡፡ ቅዝቃዜው ሲበረታማ
ሰውነታችን ሙቀት ለመፍጠር መንቀጥቀጥ ይጀምራል፡፡
የልብ ምት
የትም ሆነ የት ቢሆኑ፣ ሲራመዱም ሆነ ሲያንቀላፉ፣
ልብ በአንድ ደቂቃ ከ60 እስከ መቶ ጊዜ ይመታል፡፡
በአማካይ ልብዎ በቀን መቶ ሺህ ጊዜ ይመታል፡፡ በዚህ
ስሌት ስድሳ ዓመት አማካይ ዕድሜ ላይ የደረሰ ሰው
ከ2 ቢሊዮን ጊዜ በላይ የመታ ልብ ይኖረዋል፡፡
በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ የደም ስሮች ብዛትና
ርዝመት ጉድ ያሰኛል፡፡ ከጫፍ ጫፍ የተቀጣጠሉ 160
ሺህ ኪ.ሜ ያህል ይረዝማሉ፡፡ የደም ማጣሪያ ባይኖር
ኖሮ፣ ሰውነታችን ምን ያህል የደም መጠን
እንደሚያስፈልገው ያውቃሉ? በቀን 5,720 ሊትር! በሌላ
አነጋገር እንደ ሳንባ፣ ጉበትና ኩላሊት የመሳሰሉ የደም
ማጣሪያ የሰውነት ክፍሎች በቀን ወደ 6ሺ ሊትር ገደማ
ደም የማጣራት አቅም አላቸው ማለት ነው፡፡
ሳይፈልጉ በቀን 25ሺህ ጊዜ መተንፈስ
አልመውና አቅደው 25ሺህ ያህል ጊዜ ልተንፍስ ካሉ፣
ሌላ ነገር በፍፁም አይሰሩም፤ እንቅልፍም አይተኙም፡፡
ቀንና ሌት ስራዎ መተንፈስ ብቻ ይሆናል፡፡ ስለዚህ
አንጎላችን የመተንፈስ ልምድን አውቶማቲክ ስላደረግልን
ምስጋና ይግባው፡፡ ለመሆኑ በየጊዜው አየር ወደ ውስጥ
የምንስበውና የምናስወጣው (የምንተነፍሰው)
ለምንድነው?
የሰው ልጅ ፍጡራን በእያንዳንዷ ደቂቃ ከ200 እስከ
300 ግራም ገደማ ኦክስጅን ያስፈልገናል፡፡ ይህንን
የማያቋርጥ የአየር ፍሰት ለማስተናገድ ሳንባችን ውስጥ
300 ሚሊየን ያህል ለዓይን የማይታዩ alveali የተባሉ
የአየር ከረጢቶች ተዘጋጅተው ይጠብቃሉ፡፡

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.