Monday, September 16, 2019
Home > ማህበራዊ > በዓለም ዙሪያ ወደ 1 ቢሊየን የሚጠጋ ህዝብ በአየር ንብረት ለውጥ አደጋ

በዓለም ዙሪያ ወደ 1 ቢሊየን የሚጠጋ ህዝብ በአየር ንብረት ለውጥ አደጋ

የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም ሰላም የሰፈነባት እንዳትሆን ያደርጋል፡- ዓለም አቀፍ የሰላም ኢንዴክስ

****************

የአየር ንብረት ለውጥ ለግጭቶች ምክንያት በመሆን በደህንነት እና ሀብት ላይ በሚያስከትለው ተጽዕኖ ዓለም ሰላም የሰፈነባት እንዳትሆን ያደርጋል ሲል ዓለም አቀፍ ሰላም ኢንዴክስ አስታውቋል፡፡

እንደሪፖርቱ በዓለም ዙሪያ ወደ 1 ቢሊየን የሚጠጋ ህዝብ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎች የተጋለጡ አካባቢዎች ይኖራሉ፡፡

ከዚህ ውስጥ ደግሞ 400 ሚሊየን የሚሆኑት ሰላም በሌለባቸው አገራት እንደሚገኙ ተጠቅሷል፡፡

ከ971 ሚልዮን በላይ የሚሆነው ህዝብ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋ ስጋት ተጋርጦባቸዋል ተብሏል፡፡

በአየር ንብረት ለውጥና ግጭት መካከል ያለው ትስስር ከ25 ሰላም የላቸውም ከተባሉት አገራት በ8ቱ ላይ ለማየት እንደተሞከረው 10 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑት ህዝባቸው ከፍተኛ የአየር ንብረት አደጋ ስጋት እንደተጋረጠባቸው ተገልጿል፡፡

ከነዚህ ሀገራት ከ100 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ህዝብ በደቡብ ሱዳን፣ ኢራቅ፣ ሊቢያ፣ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ሱዳን፣ ሰሜን ኮርያ፣ ናይጄሪያ እና ሜክሲኮ አደጋ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ በስዕላዊ መግለጫው ዝቅተኛ ሰላም ካለባቸው አገራት ተመድባለች፡፡

ሪፖርቱ እንደሚያሳየው ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙ አሳዛኝ ክስተቶችን ለመቋቋም ሰላማዊ የሆኑ አገሮች የተሻለ ሁኔታ እና የተሻለ አፈፃፀም ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡

የተሻለ ሰላም አላቸው የተባሉት አገራት አይስ ላንድ፣ ኒው ዝላንድ፣ አውስትራሊ፣ ያፖርቹጋል እና ዴን ማርክ ሲሆኑ ዝቅተኛ ሰላም አለባቸው የተባሉት ደግሞ አፍጋኒስታን፣ ሶሪያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ የመን እና ኢራቅ እንደሆኑ በሪፖርቱ ተዘርዝሯል፡፡

ምንጭ፡- ስካይ ኒውስ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.