Friday, December 6, 2019
Home > ማህበራዊ > 32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ

32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ

32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነገ ይጀምራል

*********************

32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነገ በይፋ ሲጀመር አስተናጋጇ ግብፅ ዚምባብዌን ትገጥማለች፡፡

በዉድድሩ 24 ሀገራት በ6 ስታዲየሞች ለ1 ወር ያህል ይፋለማሉ፡፡

በግብፅ ባለው ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ በመጀመሪያዉና በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጫዋቾች ለ3 ደቂቃዎች እረፍት እንዲያደርጉ ካፍ ፈቅዷል፡፡

ለእርፍት የሚጠቀሟቸዉን 6 ደቂቃዎች ከመደበኛው የጫወታ ክፍል ጊዜ ካለቀ በኋላ ተጨማሪ 6 ደቂቃዎች እንዲሚጨመር መወሰኑ ነው የተገለፀው፡፡

በእርፍት ጊዜ በሜዳ ውስጥ ለሚገቡ 26 ተጫዋቾችና ዳኞች ለማቀዝቀዣ የሚሆኑ ውሀ የተነከሩ ፎጣዎችና ቀዝቃዛ መጠጦች እንደሚያዘጋጅም ነው ይፋ ያደረገው፡፡

ምንጭ፡- አፍሪካን ኒዉስ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.