Monday, July 22, 2019
Home > ዜና

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሹመት

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ፡፡ ሐምሌ 15/2011 ዓ.ም የአማራ ክልል መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው እለት መካሄድ ጀምሯል፡፡ ጉባዔው በመጀመሪያ ቀን መክፈቻው በሰኔ 15 ጥቃት ህይወታቸው ያለፈውን የቀድሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን ህልፈት ተከትሎ የተፈጠረውን የአመራር ክፍተት ለመተካት አቶ ተመስገን ጥሩነህን መርጧል፡፡

Read More

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የክብር ሜዳልያ ተሸለሙ

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጦፋ ሙሐመድ ዑመር የክብር ሜዳልያ ተሸለሙ። አቶ ሙስጠፋ የምሥራቁ ኢትዮጵያ ክፍል የለውጥ መሪ በሚሻበት ወቅት የተገኙ የቁርጥ ቀን ልጅ መሆናቸውን የገለፀው ሽልማቱን የሰጣቸው የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የሶማሌ ክልልን ሠላምና ደኅንነት በማረጋገጥ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የዕውቅና ሜዳልያውን እንዳበረከተላቸው አስታውቋል። አቶ ሙስጦፋ በሶማሌ ክልል የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር በትጥቅ ትግል ጭምር

Read More

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የክብር ዶክትሬት

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ደይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የክብር ዶክትሬት ተበረከተላቸው፡፡ ሐምሌ 13፣ 2011 ዓ.ም የአለም ጤና ድርጅት ዋና ደይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከኒውካስትል ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ከዩኒቨርሲቲው ለተበረከተላቸው የክብር ዶክትሬት በትዊተር ገፃቸው ላይ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ደይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የቀዶ ጥገና ትምህርታቸውን በኒውካስትል ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው

Read More

አውሮፕላን ላይ “ጢል” ብሎ ለመጓዝ ያሰበው ናይጄሪያዊ

አውሮፕላን ላይ “ጢሎ” ብሎ ለመጓዝ ያሰበው ናይጄሪያዊ በቁጥጥር ሥር ዋለ ......................................................................... አርብ ዕለት ሌጎስ ከሚገኘው ሙርታላ ሙሀመድ አውሮፕላን ማረፊያ ለመነሳት እያኮበኮበ የነበረ አውሮፕላን ክንፍ ላይ ተንጠልጥሎ የታየው ግለሰብ የተሳፋሪ፣ የአብራሪና የአየር መንገዱን ሠራተኞችም ልብ በድንጋጤ አቁሟል። ግለሰቡን ያዩት አውሮፕላኑ ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎች ሲሆኑ፤ ወዲያውኑ ድንጋጤያቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ጩኸታቸውን አቅልጠውታል። ከዚያም “ፓይለት አውሮፕላኑን አቁመው!”

Read More

የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ፍፃሜ

የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ፍፃሜ ዛሬ ምሽት በጉጉት ይጠበቃል በአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ፍፃሜ ሴኔጋል ከአልጄሪያ ዛሬ ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡ የሴኔጋሉ ኮከብ ሴዶ ማኔ በዛሬው ጨዋታ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ከሊቨፑል ጋር ያሳካዉን ድል ከብሄራዊ ቡድኑ ለመድገም ህልም እንዳለው ነው የተናገረው፡፡ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ እግር ዋንጫን ለማንሳት ዛሬ ከአልጄሪያ ጋር ለሚኖራት ጨዋታ ከመቼዉም

Read More

የአሐዱ ሬዲዮ ጋዜጠኞች ክስ ተቋረጠ

የኦሮሚያ ልዩ ዞን የበረክ ወረዳ ፍርድ ቤት፣ በአሐዱ ራዲዮ ጋዜጠኞች ጥበቡ በለጠ፣ ሊዲያ አበበ፣ ሱራፌል ዘላለም እና ታምራት አበራ ላይ የቀረበው የስም ማጥፋት ክስ ዛሬ ሀምሌ 12 /2011 ዓ/ም ማቋረጡን አስታውቋል። የወረዳው ፍ/ቤት ፤ ስም በማጥፋት፣ ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት እንዲሁም የብሮድካስት ህግን መተላለፍ በሚል በጋዜጠኞቹ ላይ ሶስት ክሶችን ተመስርቶባቸው ነበር። ምስክሮቻቸውን

Read More

አሜሪካዊቷ እጅ አልባ ህፃን

አሜሪካዊቷ እጅ አልባ ህፃን ሳራ ሂነስሌይ የእጅ ፅሁፍ ውድድር አሸናፊ ሆነች *************************** በአሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ነዋሪ የሆነችው እጅ አልባዋ የ10 ዓመት ህፃን ሳራ ሂነስሌይ አገር አቀፉን የእጅ ፅሁፍ ውድድር አሸናፊ መሆኗ ተዘገበ፡፡ ህፃን ሳራ ያለ ጣት ወይም ሌላ ደጋፊ ቁስ ሳትጠቀም እስክሪፕቶ ለመያዝ በመለማመድ ብቻ ነው የምርጥ እጅ ፅሁፍ ባለቤት መሆን ችላለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪም

Read More

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በጸሃይ ዘውዴ መታሰቢያ ስኮላርሽፕ ፕሮግራም

ፕሬዝዳንቷ በጸሃይ ዘውዴ መታሰቢያ ስኮላርሽፕ ፕሮግራም ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበሩ አይነስውራን ተመራቂ ተማሪዎችን አነጋገሩ ********************************* ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በጸሃይ ዘውዴ መታሰቢያ ስኮላርሽፕ ፕሮግራም ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበሩ እና በዚህ ዓመት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመረቁ ሴት አይነስውራን ተማሪዎችን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ ከተለያዩ የትምህርት መስኮች የተውጣጡት ተመራቂዎቹ በትምህርት ላይ በነበሩበት ወቅት በየሶስት ወሩ የ900 ብር ድጋፍ ሲደረግላቸው

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ለ2019ኙ የቻታም ሀውስ ሽልማት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለ2019ኙ የቻታም ሀውስ ሽልማት መታጨታቸውን ተቋሙ አስታወቀ *********************************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ለ2019ኙ የቻታም ሀውስ ሽልማት መታጨታቸውን ተቋሙ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሽልማቱ የታጩት አሳታፊ ፖለቲካንና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን በኢትዮጵያ በማምጣታቸው መሆኑን ቻታም ሀውስ ገልጿል፡፡ ታሪካዊው የኢትዮ-ኤርትራ የሰላምና የወዳጅነት ስምምነት እውን ይሆን ዘንድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጫወቱት ቁል

Read More

ኢትዮጵያውያን በሄንግሎ የ10 ሺህ ሜትር ማጣሪያ አሸነፉ

ሀጎስ ገ/ህይወትና ለተሰንበት ግደይ በሄንግሎ የ10 ሺህ ሜትር ማጣሪያ አሸነፉ ********************************** ትላንት በኔዘርላንዷ ከተማ ሄንግሎ በተካሄደ የመጣሪያ ውድድር አትሌት ሀጎስ ገ/ህይወት የ10 ሺህ ሜትር በ26፡48.95 ደቂቃ በመግባት ቀዳሚ ሆኖ ገብቷል፡፡ በውድድሩ ሰለሞን በረጋ በ26፡49.46 ደቂቃ 2ኛ፣ ዮሚፍ ቀጄልቻ በ26፡49.99 ደቂቃ 3ኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡ በርቀቱ የሴቶች ውድድር ለተሰንበት ግደይ በ30፡37.89 ደቂቃ ቀዳሚ ሲትሆን፣ ነፃነት ጉደታ

Read More